የስትራቴጂክ ዕቅድ የማስተዋወቂያ መድረክ በአዳማ ተካሄደ::

Undefined

ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ የአምስት አመት (ከ2014-2018ዓ.ም) ስትራቴጂክ ዕቅድ የማስተዋወቂያ መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ:: በመድረኩ የክልሎች ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ማህበራት ጥምረት ተወካዮች ተገኝተዋል:: በመድረኩ ስለአዲሱ ስትራቴጂክ እቅድ ለተሰብሳቢዎች ገለጻ የተደረገ ሲሆን ስትራቴጂክ ዕቅዱ ኤችአይቪን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እ.ኤ.አ. በ2025 ለማሳካት የተቀመጠውን የሶስቱ 95 ለማሳካት እንዲያመች ተደርጎ በከፍተኛ ጥንቃቄና ጥራት የተሰራ መሆኑ ተገልጿል::
በፌደራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዕቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ነጻነት ሀኒቆ ስለአዲሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት እቅዱ ከሰነድነት በዘለለ መሬት ላይ ወርዶ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ለውጥ ማምጣት እንዲችል የእያንዳንዳችንን አስተዋጽኦ የሚጠይቅ ነው ብለዋል::
በዚሁ መደረክ ላይ የማይታይ መጠን=የተገታ መተላለፍ ንቅናቄ ለማህበራቱ ጥምረት ተወካዮች ገለጻ የተደረገ ሲሆን በቀረበው ገለጻ ላይ ውይይት ተካሂዷል::
ባሳለፍነው ሳምንት “በደሜ ውስጥ ያለውን የኤችአይቪ መጠን በመቆጣጠር፣ ስርጭቱን እገታለሁ!” በሚል መሪ ቃል በደብረብርሀን ከተማ በይፋ የተጀመረው የማይታይ መጠን=የተገታ መተላለፍ(የ=የ) ንቅናቄ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች የህክምና ባለሙያዎችን ምክር በተገቢው ሁኔታ በማዳመጥ እና የሚነገራቸውን ተግባራዊ በማድረግ በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን የቫይረስ መጠን በመቀነስ የቫይረሱን ስርጭት መግታት የሚቻል መሆኑ ተገልጿል::

Posted on: 
Wednesday, March 31, 2021
Alarm: 

Add new comment