ኤችአይቪን ለመከላከል ይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታላሚ አድርጎ መስራትእንደሚገባ ተገለጸ፤

Undefined

ይህ የተገለጸው በደብረብርሀን ከተማ ሀገራዊ የኤችአይቪ ኤድስ የአምስት አመት ስትራቴጂ እቅድ የማስተዋወቂያ መድረክና የሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ ዘርፈብዙ ምላሽ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም በተለምዶ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከሚሰራው ስራ በመላቀቅ ይበልጥ ተጋላጭና ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በለየና ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሆን እንዳለበት የገለጹት ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ የፌደራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ይበልጥ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ሴተኛ አዳሪዎች፣ የህግ ታራሚዎች፣በመርፌ የሚወሰዱ አደንዛዥ መድሀኒቶች የሚጠቀሙ ሲሆኑ ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የተፋቱ ወይም የትዳር አጋራቸው የሞተባቸው፣ረዥም ርቀት የመኪና አሽከርካሪዎች፣ ከፍተኛ የኤችአይቪ ስርጭት ያለባቸው ቦታዎች የተሰማሩ ሰራተኞች፣ታዳጊ ልጃገረዶችና ወጣት ሴቶች፣ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች የጾታ አጋሮች ናቸው፡፡ እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች ከአጠቃላዩ ማህበረሰብ የተለየ ትኩረት ሰቶ መስራት እ.ኤ.አ. በ2025 ለማሳካት ለታቀደው ሶስቱ 95 ማሳኪያ መንገድ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሀገራችን በአሁኑ ጊዜ የኤችአይቪ ስርጭቱ ከፍተኛ የሆነባቸው 265 ወረዳዎች የተለዩ ሲሆን ለነዚህ ወረዳዎች የተለየ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባ እና ብዙ ተለፍቶበት የተዘጋጀው ሀገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ ስትራቴጂክ እቅድ (2014-2018 ዓ.ም) ሼልፍ ላይ እንዳይቀር እና ወደተግበር እንዲወርድ የሁሉንም አካላት ርብርብ እንደሚጠይቅ ተገልጿል፡፡ በመድረኩ ላይ ለስትራቴጂክ እቅዱ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ሰርተፍኬት ተሰቷል፡፡

Posted on: 
Tuesday, March 23, 2021
Alarm: 

Add new comment