33ኛው የአለም ኤድስ ቀን በትላንትናው ዕለት በቦሌ ለሚ የኢንዱስትሪ ፓርክ ተከብሮ ውሏል

Undefined

“ኤች አይቪ ኤድስን ለመግታት አለም አቀፋዊ ትብብር የጋራ ሀላፊነት!” በሚል መሪ ቃል በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተከበረበት ወቅት የጤናው ሴክተር አመራሮች፣ የማህበራትና ጥምረት አመራሮች፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሀላፊዎች፣ የባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮችና የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሰራተኞች ታድመዋል፡፡
በሀገራችን የጠቅላይ ሚንስትሩን የማዕድ ማጋራት ጥሪ ተከትሎ በችግር ላይ ላሉ ወገኖች የተጀመረው የማዕድ ማጋራት ኤች አይቪ በደማቸው ለሚገኝ እና እርዳታ ለሚያሻቸው ወገኖች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች የፀረ-ኤችአይቪ መድሀኒቱን ያለማቋረጥ እንዲወስዱ በአጋርነት መንፈስ ሁሉም ባለድርሻ አካል መንቀሳቀስ እንዳለበት ተገልጿል፡፡ በመድረኩ ላይ ከአጋር ድርጅቶች ኢትዮጵያ ለኤችአይቪ የሚሰጡ ፈንዶችን ለተገቢው እርዳታ በማዋል ለሌሎች ሀገራት አርአያ እንደሆነች ተገልጿል፡፡
በበዓሉ ማጠቃለያ ላይ የበዓሉ ታዳሚዎች “ደማችን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል የደም ልገሳ አከናውነዋል፡፡

Posted on: 
Wednesday, December 2, 2020
Alarm: 

Add new comment